የአዲስ አመት በረከት
ኦቪድ ሪል ስቴት በአራት ኪሎ ጥይት ቤት ሳይት ቤቶቻቸውን ገዝተው ሙሉ በሙሉ የተረከቡ ባለቤት ደንበኞቹ መሀከል በመገኘት አዲስ ዓመትን በማስመልከት ልዩ ድንገተኛ (Surprise) ሽልማት አበረከተላቸው!
የኦቪድ ሪል እስቴት የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት ክፍል ሀላፊ አብይ ንጉሴ እና የሽያጭ ዲፓርትመንት ክፍል ሀላፊ ኤርሚያስ ሙሴ ከኢትዮጵያ ሴት አርቲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ልዩ ገዙ እና ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር በመሆን የኦቪድ ሪል እስቴት ሳይቶችን እና ደንበኞችን ጎብኝተዋል።
በዚህ ጉብኝት፣ በኦቪድ 4 ኪሎ ጥይት ቤት ሳይት ከታቀዱት 8 መደበኛ ብሎኮች ውስጥ 3ቱን ለደንበኞች በማስረከብ እና አሁንም በግንባታ ላይ ያሉትን ቀሪ 5 ብሎኮች በቅርቡ ባስመጣው የኩም ካንግ አልሙኒየም ፎርም ወርክ በመታገዝ በ 2019 ለማስረከብ በተለመደው የ24/7 የስራ ባህሉ እየሠራ የሚያደርገውን የግንባታ ሂደት ቦታው ላይ እንዲመለከቱ ተደርጓል።
በተጨማሪም፣ ኦቪድ ሪል እስቴትም ደንበኞችን በመኖሪያ ቤታቸው በመጎብኘት ለአዲስ ዓመት በዓል የተዘጋጁ ስጦታዎችን በማበርከት የአዲስ አመት መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ጉብኝቱም በቦሌ መድሀኔዓለም እና ቦሌ ቡልቡላ O.G.G.C ሳይቶች ቀጥሎ ማህበሩ የግንባታ ሂደቱን በቀጥታ የተመለከቱ ሲሆን በቀጣይ የሚኖሩ የግንባታ ሁኔታዎችና እቅድ እንዲረዱ የሳይት ጉብኝትና ዝርዝር መረጃ ተሰጥቷቸዋል።
ይህ ልዩ ጉብኝት የደንበኞች በኦቪድ ቤት አኗኗር እና የግንባታ ሳይቶች መረጃዎች በተለያዩ የቴሌቪዥን ቻናሎች የአዲስ ዓመት የበዓል ፕሮግራም ላይ እንዲሁም በኦቪድ ሪል እስቴት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይቀርባሉ።
ይጠብቁን! ብዙ አስደሳች ዜናዎች በቅርቡ!
የጉብኝቱ መርሃ ግብር በኦቪድ ሪል እስቴት ዋና መስሪያ ቤት በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰናይ ሸዋፈራው የእንኳን አደረሳችሁ እና የመዝጊያ ንግግር ተጠናቋል።
በመጨረሻም ለኢትዮጵያ ሴት አርቲስቶች ማህበር ለሰጡን ውድ ጊዜ እና ላጋሩን መልካም ምኞት ምስጋና በማቅረብ ኦቪድ ሪል እስቴት 100,000 ብር የአዲስ ዓመት ስጦታ ለኢትዮጵያ ሴት አርቲስቶች ማህበር አበርክቷል።
ኦቪድ ሪል እስቴት አሁንም በ4 ኪሎ ጥይት ቤት፣ በጉለሌ ፣ በቦሌ ቡልቡላ O.G.G.C ሳይት፣ በጫካ ፣ በቦሌ መድሀኔዐለም እና በቦሌ ጃፓን ላይ የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ሡቆችን እየሸጠ ይገኛል።





